top of page
Search

ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አክሲዮን ማኅበር ዋሊን የተሰኘ አዲስ የቢራ ምርት ለገበያ አቀረበ

በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ ከ88 ሚሊዮን ዩሮ በላይ በሆነ መነሻ ካፒታል ዘመናዊ የቢራ ፋብሪካ በማቋቋም ከሶስት አመት በፊት ስራውን በይፋ የጀመረው ድርጅታችን፤ የማምረት አቅሙን የሚያሳድግ የፋብሪካ ማስፋፊያ ማጠናቀቁን እንዲሁም የአዲሱን የዋሊን ቢራ ወደገበያ መቅረብ በማስመልከት በስካይላይት ሆቴል ደማቅ ፕሮግራም አካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ታዋቂ አርቲስቶችና የንግዱ አለም ሰዎች የተገኙ ሲሆን የኦሮምኛ ቋንቋ ስያሜ ያለው አዲሱ ዋሊን ቢራ ለታዳሚዎች የማስተዋወቅና የቅምሻ ፕሮግራም ተደርጓል።

አዲሱ ዋሊን ቢራ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለውን ተጠቃሚ ማዕከል አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ ኡርጌሳ ምርቱ ለገበያ ከማቅረቡ በፊት በ6 ትላልቅ የኦሮሚያ ከተሞች በሚገኙ ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ አባላት ከቢራው ጥራት ጀምሮ እስከ አስተሻሸግና ልዩ ምልክቶች ድረስ አጠቃላይ የምርቱ ሁኔታ እንዲገመገም መደረጉን ገልፀዋል። መቶ በመቶ ተፈጥሯዊ ከሆኑ ግብዓቶች የተጠመቀ እና ምንም አይነት ስኳር የማይጨመርበት አዲሱ ምርት አብሮነትን ለማወደስና ለማድመቅ በአብሮነት የተጠመቀ እንደመሆኑ ህዝባችን እንደሚቀበለው እርግጠኞች ነን ሲሉም አክለዋል።

በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ ዩናይትድ ቤቨሬጅስ ከተመሰረተ አጭር ጊዜው ቢሆንም በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ግብር ከፋይ መሆኑ እና በስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በልዩ ልዩ የልማት ስራዎች እያደረገ ያለው ተሳትፎ በአርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልፀው ወደፊትም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ስራዎች ላይ ድርጅቱ ያለው አጋርነት ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል።

ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አክሲዮን ማህበር በካንጋሮ ፕላስት እና በዩናይትድ አፍሪካ ቤቨሬጅስ ጥምረት እ.ኤ.አ በ2016 የተመሰረተ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። ካንጋሮ ኢንደስትሪያል ግሩፕ ወይንም ይርጋ ኃይሌና ቤተሰቦቹ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሪል ስቴት፣ በኢምፖርትና ኤክስፖርት ንግድ፣ በግብርናና መሰል የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ተሰማርቶ ላለፉት 58 ዓመታት በሀገራችን ሲሰራ የቆየ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።


88 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page